/አደም ሙሃመድ/
መቼም የቦሌ ልጅም ይፎርፋል ወይ እንዳትሉኝና አንድ ቀን ከጓደኛቻችን ጋ ትምህርት ፎረፍንና ቦርሳችንን የሆነ ሱቅ አስቀምጥን፡፡

ከዛ የት እንሂድ? ተባባሉ አሰቡ... አሰቡ... አሰቡና ሁለቶች 'ጎላጉል' አሉ ሶስቶች 'ኤድናሞል' እኔ ደግሞ 'ደሀ ሀሳብ መሰንዘር ሳይሆን በሀብታሞች
ሀሳብ መስማማት ነው ያለበት' አልኩኝ በልቤ ምክንያቱም ሀሳብን ቢሰነዝሩት ቡሃላ መዘዙ ሂሳብ ነውና እንደ እሱባለው 'የትም ይመቸኛል' ልላቸው ወሰንኩ
እነሱ የኔን ሀሳብ ሳይሰሙ 'meter taxi' ሊጠይቁ ሄዱ እስኪ አሁን ሀሳብ ልሰንዝር ብየ "እ በእግር ወክ እያደረግን ብንሄድ አይሻልም 10 ደቂቃ
አይሆንምኮ" አልኳቸው
.
ተስማምተን በእግር መጓዝ እንደጀመርን V8 መኪና(እኛ ስሙን እንጥራ መንዳቱን ግን እነሱ ይንዱት) ሲመጣ "ዳድ ነው ደብቁኝ በናታችሁ ፕሊስ" ብሎ ከመሀላችን ገባ መኪናውም አለፈ ዳድም አልነበረም ስለመምህሮች እያወራን ልንደርስ ስንል ደግሞ የፕሌን ድምፅ ሲሰማ ሌላኛው ደግሞ " ኦ ማይ ጋድ ጋሸ ነው ምን ይዋጠኝ ያየኛል ከሩቅ ነው የሚለየኝ" አላለም "እንዴ አውሮፕላን ነውኮ መኪና አይደለም" አልኩት " እኮ የአባቴ ፕሌን ነው ድምፁ ይለየኛል" እሺ ይሁን ጋባዥ አንተ አይደለህ ብየ የተቀደደ ዩኒፎርም
ጃኬቴን ከራሱ ላይ ጣል አደረኩለት "ምንድን ነው ?" አለኝ "አየህ ድንገት ቢያይህ እንኳ ይሄ የድሀ ልጅ ነው የኔ ልጅ አይደለም ብሎ ያልፍሀል" ስለው ቀና ብሎ አየና
"ኦህ ቴንኪው ጋድ " አለ
"ምነው" ስለው
"የጋሼን ፕሌን ዘበኛችን ነው አሁን እየነዳው ያለው ቀና ብየ ሳይ ታየኝ ጋሼ ውስጥ የለም፡ አያቴ ቤት ቡና ጠጡ ሊል ተልኮ ነው፡፡" ሲለኝ
እንደ አልጀርሱ ስምምነት "ይሁና" ብየ ዝም አልኩ
.
ኤድናሞል ልንገባ በሩ ላይ ስንደርስ "እንዴ እንዴ አባቴ ታክሲ ውስጥ" ስላቸው አላመኑኝም 'የሰው ልጅ ታክሲ ውስጥ ምን ይሰራል' ብለው አስበው ይሆናል
"ወላሂ እውነቴን ነው" አልኳቸው
"እንዴ ታክሲ ውስጥ?"
"አዎ"
"መኪና የለውም?"
"ኧረ አለው ብዙ መኪኖች ነበሩት ለንደን ለስራ ሲመላለስ ፓርኪንግ ውስጥ እንዳስቀመጣቸው በዛው ይረሳቸውና ትዝ ሲለው ለማምጣት ሼም ይይዘዋል" አልኳቸው ማን ከማን እንደሚያንስ እናያለን ብየ