(አቡዘር አደም)
.
አ.አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመግባቴ በፊት ይመስለኛል 9ኛ ክፍል ላይ ከጎጃም እንደመጣሁ የሆነ ትምህርት ቤት ገባሁ ገና እንደገባሁ ራስህን አስተዋዉቅ ተባልኩ እንደምንም ወኔ አሰባስቤ

"ማይ ኔም ኢዝ 'ሰው ባይሞት ሞትባይኖር' አይ ካም ፍሮም ቡሬ ቡሬ ኢዝ ዲባይዲድ ኢን ቱ ቱ ታይ ቡሬ ኤንድ ላይ ቡሬ ታንኪው" ብየ ቁጭ ልል ስል የተማሪውን ፊት ስቃኘው እዝጎ ያስብላል ኮሶ የጠጣች የጉራጌ ሙሽራ መስለዋል
.
መምህሩ 'ማን አልከን ስምህን' ሲለኝ "ሰው ባይሞት" አልኩት የሀምሌን ሰማይ መስሎ የነበረው ፊት ሁላ በሳቅ ፍስስስ አለ ግራው ገባኝ 'ያባትህስ' አለኝ 'ሞት ባይኖር ቢኖር መሸሻ ' አልኩት
አሁንም ሳቁ አንገቴን ደፋ አድርጌ ተሳሳትኩ እንዴ? ብየ ማሰብ ጀመርኩ ሳስበው ምንም አልተሳሳትኩ ስማችን ለምን እንዲህ እንደሆነ ሲጠይቀኝ የጎጃም ህዝብ ለሰው ያለው ፍቅር ነው ሰው ባይሞት
ጥሩ ነበር ብሎ ስለሚያስብ መሆኑን ነገርኩት፡፡
.
በሶስተኛው ቀን አርፍጀ መጣሁና ሳንኳኳ መምህሩ እያስተማረ ነበር እና ስላንኳኳሁ የተናደደ መሰለኝ (ድሮ ከተማርኩበት ት/ት ቤት ደግሞ ሳያረፍዱ መምጣት ዘበት ነው) መምህሩ ብቅ አለና ፊቱን አጨማዶ ኮስተር ብሎ
"ጌቲንግ" ሲለኝ 'ውጣ!' ያለኝ መስሎኝ ወደ ቤቴ ተመለስኩ (እስከዛሬ አልገባኝም ነበር)
.
ከሳምንት በሁዋላ የዕውቀቴ ባዶነት ግራ ግብት ያለው መምህር 'ሰው ባይሞት' አለኝ 'አቤት ቲቸር' 'ሃው ኦልድ አር ዩ?' አለኝ የማውቃትን ስለጠየቀኝ ደስስስ ብሎኝ ፈጠን ብየ ''አይ አም ፋይን ታንኪው ኤንድ ዩ ቲቸር?"
አሁንም ሳቁ ተማሪዎች እንዳልተሳሳትኩ እርግጠኛ ስለሆንኩ በቃ አመላቸው ነው ብየ የነሱን ነገር ተውኩት፡
.
በሁለተኛው ሳምንት
እነዚህ ባማርኛ ፃፋቸው ብሎ ወረቀት ሰጠኝ መምህሩ
1. History
2.Knowledge
3.Dinosaurs
ያው የጎጃምን እንግሊዘኛ ታውቁት የለ እንደምንም ተጨናንቄ
1.ሃይ እስቶሪ
2.ከነዋለ ደጅ
3. ዳኛቸው አስረስ
ብየ መለስኩለት
ወረቀቱን አይቶ ተከተለኝ ብሎ ወደ ቢሮ ይዞኝ ሄደ እና 'ለዚህ ትምርት ቤት አትመጥንም' ብሎ ወደቤቴ ሸኘኝ
.
እና እንዴት ዩኒቨርሲቲ ገባህ ካላችሁኝ ከዛማ ወደጎጃም ተመልሼ እንደፈለኩ እማረፍድበት እማልሳቀቅበት ት/ት ቤቴ በሰላም ገብቼ ያዲስ አበባው መምህር ለዚህ ትምርት ቤት አትመጥንም ቢለኝም
መቼም የጎጃም ሰው ደግ ነውና ለአዲስ አበባ እምበርስቲ ትመጥናለህ ብሎ እኔንና መሰሎቸን ልኮን ይሄው አለን እላችሁዋለሁ፡፡