በአፋር ክልል ጨው ማምረቻ ይዞታውን እና ግብርም ይከፍልበት የነበረውን ቦታ በአፋር ክልል መንግሥት መቀማቱን የኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅ እና ባዮ ፊውል ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ እንደገለፀው ከሆነ የአፋር ክልል ማዕድን ቢሮ “አልተጠቀማችሁበትም” በሚል ምክንያት የጨው ማምረቻ ቦታውን እንደነጠቁው ለማወቅ ተችሏል።
በኢትዮጵያ ማዕድን ነዳጅ እና ባዮ ፊውል ኮርፖሬሽን
እቅድ መምሪያ ኃላፊ እና የአፋር ጨው ማምረቻ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስኪያጅ ይድነቃቸው ተፈራ፤ ከተቋቋመ ወደ 18 ዓመት ገደማ የሆነው የጨው ማምረቻው በመንግሥት የሚተዳደር እንደሆነና 10 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሆን ቦታ ተሰጥቶት አንደነበርም ተናግረዋል።
ይህን መረጃ November 17 / 2020
ያወጣው ኢትዮጵያ ነገ ዜና የተባለ ድረ ገፅ ሲሆን የጨው መሬቱ በአፋር ክልላዊ አስተዳደር የተወሰደበት የኢትዮጵያ ማዕድንና ነዳጅ ኮርፖሬሽን አልተጠቀማችሁበትም ተብለው የተነጠቁትን የጨው መሬት ለምን ሳይጠቀሙበት እንደቀሩ የተናገረው ነገር የለም::