ድንቅ መረጃዎች ናቸው በአቢቹ ለህዝብ እንደራሴዎቹ በዝርዝር የቀረቡት::
አቢቹ ደጋግሞ እንደሚለው እኛ ኢትዮጵያውያን ነገር የመርሳት ችግር ስላለብን እንጅ የምክር ቤት አባላቱ እንኳንስ የመንግስት የጦርነት ውሎ ሪፖርት ሊነገራቸው ይቅርና የሜቴክን በጀት ለመጠየቅም ፈቃድ አልነበራቸውም ::

በኢትዬ ኤርትራ ጦርነት ስለሆነው ነገር ለምክር ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ በወቅቱ የነበሩት ጠ/ሚር መለስ ያኔ የሰጡት መልስ _ እባብ ያየ _ እንደሚባለው የምክር ቤት አባላቱን በማስደንገጥ እና እዚያው ድንጋጤ ውስጥ እንዲኖሩ ካደረጋቸው አመታት ተቆጥረዋል : ለውጡን ትተን ማለቴ ነው ::
እናቴ , ከለውጡ በኃላማ ያለው አይነገር ! ሁሉ የፖርላማ አባል ተናጋሪና ጠያቂ ሆኗል:: እሰየው ነው ::
ስለ ምክር ቤት አባላቱ ሳስብ አንዳንዴ ይገርመኛል ! ምክንያቱም አቢቹ ወደ ስልጣን ከመጣ በኃላ የህዝብ እንደራሴ በመሆን ወደ ምክር ቤቱ የመጡ እንጅ ለአመታት የድጋፍ እጅ ሲያወጡ የኖሩ አልመስልህ እያለኝ:: መለወጣቸውን ተቃወምኩ አላልኩም ! ተገረምኩ ነው ያልኩት ::
ከለውጡ በኃላ አቢቹ ወደ ምክር ቤት ሪፖርት ለማቅረብ ብቅ ባለ ቁጥር በእንደራሴዎቹ የሚቀርቡት ጥያቄዎች የሚያነቃቁ ናቸው, ምንም እንኳ ጥያቄዎቹ በምክር ቤቱ ፅ/ቤት በኩል አስቀድሞ የታወቀና ለመላሹ የደረሰ ቢሆንም ማለቴ ነው ::
* የሰሜን ዕዝ ሰራዊታችን ላይ ይህን መሰል ጥቃት ሲደርስ መንግስት እንዴት መረጃ አልነበረውም?
* የህወሐትን ሁኔታ በመመልከት እንዴት በመንግስት በኩል ቅድመ ዝግጅት አልተደረገም?
* ህወሓት ስለምን ሽብርተኛ ቡድን ተብሎ አይከሰስም?
* የህወሓትን ቡድን በመርዳት በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት እንዲደርስ በተባበሩት ወታደሮች ላይ የተከፈተው ክስ በወታደራዊ ፍ/ቤት መታየት ሲገባው ለምን በመደበኛው ፍ/ቤት እንዲታይ ሆነ ? ወዘተ ወዘተ ወዘተ ብዙ ጥያቄዎች ከም/ቤት አባላቱ ወደ አቢቹ ቀረቡ::
የአብዛኛው የም/ቤት አባላት ጥያቄ ሲታይ ተመሳሳይነት ያላቸው ጉዳዬች ላይ ትኩረት ያደረጉ እና ባለፉት ሁለት አመታት ህዝብ ሲሞትና ሲፈናቀል መንግስት ደካማ በመሆኑ ዜጎችን መጠበቅና እርምጃ መውሰድ አልቻለም : የህወሐት ድፍረትም ከዚህ የመነጨና አሁንም የመንግስትን ጥንካሬ ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው የሚሉ ጥቅል ሀሳቦችን የያዘ ነው ::
የምክር ቤት አባላቱ በለውጡ ሳቢያ የቀመሷትን ነፃነት በመጠቀም አቢቹ ላይ የጥያቄ ናዳ አዘነቡ::
የምክር ቤት አባላቱ ውሎ መነቃቃት ቢያስደስትም እንደራሴዎቻችን ግን በኢህአዴግ ውስጥ ለሆነው ለውጥ ብዙም እውቀት እንደሌላቸውና ከሂደቱም የራቁ መሆናቸውን : ይህም ብቻ ሳይሆን ዛሬም ያለውን ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ ትንታኔ ውስጥ ያላስገባና ህወሓት ያደረሰውን ግፍ በማየት ብቻ እንደራሴዎቹ በቁጭት ያቀረቧቸው ጥያቄዎች ናቸው::
የአቢቹ መልሶች የዋዛ አልነበሩም :: ለውጡ የመጣበትን የትግል ሂደት : የደህንነቱን አቅም : እንኳንስ ሀገር ላይ መወሰን ይቅርና የግል ጠባቂውን መምረጥ እንዳልቻለ አቢቹ ገብስ ገብሱን መለሰ:: ሌሎቹ ጥያቄዎች በጥቅል ተመለሱ::
አቢቹ በጥቅል የመሰበትን ምክንያት ብንፈትሽ ያለ ነገር እንዳልሆነ ይገባናል: :
በእንደራሴዎቹ ቁጭት ለተነሱ ለሁሉም ጥያቄዎች በዚያው ልክ መልስ መስጠቱ ፖለቲካዊ : አካባቢያዊ እንዲሁም አሁን ባለው ሂደት ላይ የሚያመጣውን ጣጣ የሚያንር ቢሆንስ ? አቢቹ እራሱንና ቤተሰቡን መጠበቅ በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ እንደነበር የማያውቁት የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት በቁጭት ላነሷቸው ለሁሉም ጥያቄዎቻቸው የሚሰጠው ምላሽ ይዞት የሚመጣውን ፓለቲካዊ ጣጣ እንደምን መተንተን ይችላሉ ? መተንተን ቢችሉማ ኖሮ ብዙ በአደባባይ የማይነሱ ጥያቄዎችን ባላነሱ ነበር ?


Follow Us