የሀገር መከላከያ ሰራዊት በባዶ ሲደነፋ : ከህግ በላይ ነኝ ባዩን ሽፍታውን የወንበዴ ቡድንን ከነጀሌዎቹ እየጠራረገ መቀሌን ሙሉ ለሙሉ መግባቱ ከተሰማ በኃላ የህወሐት ደጋፊ ተስፈኞች አዲስ ነጠላ ዜማ እያሰሙ ነው :: " ህወሓት ተጠናክራ ትመለሳለች " የሚል የቂላቂል ዜማ !!

በህወሐት የዝርፊያ ሰንሰለት ውስጥ ታቅፈው ሀገርና ህዝብ በመዝረፍ የደም ገንዘብ ሲያጋብሱ የኖሩ ዘራፊዎችና የእነ ኦነግ ሴራ ዘዋሪዎች የሽብር ቡድኑን መደምሰስ ለመቀበል በፍፁም አልሆነላቸውም::
የኢ/ት መንግስት ጦር ህዝብ ሲሽነግል ነው እንጂ የእውነት የህወሓት ቡድንን ድል አድርጎ ከሆነ ለምን ተፈላጊ የተባሉትን ሰዎች ይዞ አላሳየም ? የሚል የጅል ጥያቄ ይዘው ያላዝናሉ !!
ተስፈኞቹ ጨምረውም ብዙ ሲያቅራራ እና የትግራይ ምድር የመከላከያ ሰራዊቱ መቀበሪያ ይሆናል እያለ ይለፍፍ የነበረውና በቀላሉ ሽሽቶ ድል የሆነውን የህወሐትን ፕሮፓጋንዳ እንዳዲስ በመያዝ ጀግንነቱን ሊነግሩን ይሞክራሉ :: በተፈጥሮ አቀማመጣቸው ብቻ ለውጊያ ፈታኝ የሆኑ የትግራይ ተራሮችን በጥቂት ቀናት አውደ ውጊያ በመከላከያ ሰራዊት የተነጠቀውን የሽብርተኛውን ቡድን አቅም ያሳየና ህወሓት ምን ያህል ደካማ እንደሆነ አስቀድሞ ያሳዬ ቢሆንም ለቡድኑ ተላላኪዎች ግን የሚዋጥ አልሆነም:: ህወሓት አስቀድሞ ባወራው መጠን ቢሆን ኖሮ አቅሙና የጦር ዝግጅቱ የተፈጥሮ ምሽግ በሆኑ የትግራይ ተራሮች ታግዞ የመከላከያ ሰራዊቱን ለጥቂት ጊዜም ቢሆን መመከት በቻለ ነበር ::

ዳግም ቀና እንዳይል በመከላከያ ሰራዊቱ አከርካሪውን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የተመታውን ቡድን ዛሬም በእውር ድንብር አጀግነው እና በህይወት ያለ አስመስለው ተላላኪዋቹ እና የጥቅም ተጋሪዎቹ የሚያወሱት ህወሓት በተስፋ መቁረጥና በሽሽት መሀል ሆኖ ወደ አስመራ ያደረገውንና ኢላማ አልባ የሆነውን የሮኬት ተኩስን እንደ ድል በመቁጠር ጥንካሬውን ሊነግሩን ይከጅላሉ ::

የሚገርመው ነገር ከተስፈኞቹ እና ከህወሐት ቡችላ ፕሮፓጋንዲስቶች መሀከል ጎልተው የሚሰሙት ደግሞ ላለፉት 27 አመታት በህወሐት ሲቀጠቀጡና የእስር ቤት ቋንቋ ኦሮምኛ ሆኗል እስኪባል ድረስ በጅምላ ሲታጎሩ የኖሩ የኦነግ አባላትና ደጋፊዎች መሆናቸው ነው ::

አንዴ ኦነግ : አንዴ ጠባብ : ሌላ ጊዜ የእከሌ ተላላኪ እያለ ህወሓት ስጋቴ ናቸው ላላቸውና ለጠላቸው ቡድኖች የዳቦ ስም እያወጣ በሰብአዊ ፍጡር ላይ የማይደረግን ስቃይና በደል ሲፈፅም እንደ ኖረ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከለውጡ በኃላ በአደባባይ በመግለፅና የህወሐትን ነውረኝነት በመናገር ለሆነው ሁሉ በመንግስታቸው ስም ይቅርታ በመጠየቅ እስረኞችን ቢፈቱም የህወሐት ቅጥቀጣውና አፈናው ለምን ቀረብን ያሉ የኦነግ እና የኦሮሞ ፖለቲከኞች ነበሩ በዋናነት አብይን በመቃወም ከገራፊያቸው ከህወሐት ጎን የቆሙት::

ለውጡን በመቃወምና ሀጥያተኛውን ቡድን በመደገፍ የገራፊያቸውን ድግስ ለመብላት መቀሌን ተመላልሰው ሲሳለሙ የከረሙት ሙት ፓለቲከኞች እና የዘራፊው ቡድን የጥቅም ተቋዳሾች የእንጀራ አባታቸው ግባተ መሬት ከታወጀም በኃላ ከመቃብር አፋፍ ሊያድኑት የሀይማኖትና የዘር ጭፍጨፋ ለማስነሳት ብዙ ወንጀል በመፈፀማቸው ዋነኞቹ ወህኒ ወረዱ የተቀሩትም በህጋዊ ፓርቲነት ሰበብ ለውጡን ለመቀልበስ ማሴራቸውን ሀገር አውቆ ተፋቸው ያም ሆኖ ወንጀለኛው ላይ እርምጃ ከተወሰደም በኃላ ውስጥ ለውስጥ ዛሬም የጡት አባታቸው ይመለስ ዘንድ ዝባዝንኬ ፕሮፓጋንዳቸውን ተያይዘውታልና መንግስት ለሀገር መፅናትና ለዜጎች ሰላም ሲል እነዚህን ርዝራዦች ከህወሐት ባልተናነሰ እርምጃ ልክ ማስገባት ቀጣዩ ስራው ሊሆን ግድ ይለዋል::

የህወሐት የሚሊሻና የልዩ ሀይል ስብስብና አሮጌ መሪዎቹ አስቀድመው የሰራዊቱ መቀበሪያ ይሆናል ባሉት የትግራይ ምድር ዳግም ላያንሰራሩ የተቀበረው ተቀብሯል : የሽሽው በህይወት ቢያዝም ሆነ እንደሽሽ ቢቀር እሱ ግድ አይሰጥምና ተስፈኞቹን ልክ ማስገባት አስፈላጊ ነው::


Follow Us