ይህንን ትውልድ የሚያምሰው እና ሀገርን ሰላም የነሳው ማነው ከተባለ ? መልሱ አንድ እና አንድ ነው :: እሱም ያ ትውልድ ነው :: የ60ዎቹ ፖለቲከኞች ክፉ ትውልድ::

ለዚህ ማስረጃ ፍለጋ ርቆ መሄድ ምንም አያስፈልግም : በቀላሉ ከ40 አመታት በፊት በአስተሳሰብ ጎራ ለይተው ለመጠፋፋት የሚፈላለጉና ዛሬም በህይወት ያሉ የኢሀፖ : የህወሀት : የኦነግ : የመኢሶን ወዘተ ወዘተ ፖለቲከኞችን መመልከት ከበቂ በላይ ነው::
እነዚህ ክፉ ፖለቲከኞች ያኔ በተማሪ ቤት ህይወታቸው ይበሻሽቁበት : ይናናቁበት የነበረን የግል ጥላቻቸውን መሬት ላራሹ : የብሔር እኩልነት : የሰራተኞች መብት ይከበር : አብዬታዊነት ለውጥ ወዘተ : ወዘተ በሚል ተቧድነውና ፓርቲ መስርተው ትግል ቢጀምሩም አስገራሚው ነገር ሊታገሉት ከወጡት ሀይል ይልቅ መገዳደል የጀመሩት በቅድሚያ እርስ በርስ ነበር ::
ይህ መሆኑን ደግሞ በመፅሐፎቻቸው ያስነበቡን እራሳቸው ናቸው : መጽሐፍ ፅፈው ጉዳቸውን እንድናነብ ማድረግ ብቻም ሳይሆን ሰዎቹ ዛሬም በአንድ አዳራሽ ውስጥ አብረው ለመቀመጥ እንኳ የማይፈቅዱ እና ክፉ የቂም በቀል መርዝ በልባቸው ውስጥ የተተከለ እርጉሞች መሆናቸውን በየአጋጣሚው እያየን ነው::
ከ40 ምናምን አመታት በፊት በልባቸው የነበረና በዘመን ብዛት መዘመን ያልቻለ አሮጌ የፖለቲካ አስተሳሰባቸውን ይቅር ካላሉት የርስ በርስ ጥላቻና መናናቅ ጋር ይዘው : በዘመኑ ወጣት እጣ ፈንታ ላይ ዛሬም መቆመር ይፈልጋሉ::
የስድሳዎቹ የፖለቲካ ሰዎች የፖለቲካ ቁማርና የርስ በርስ መናናቅ እንዲሁም ጥላቻቸውን ይቅር ተባብለው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ መቃብር በመሽኘት ለእነሱም ለሀገርም ፈወስ እንዲሆን ከመስራት ይልቅ ዛሬም አንድ እግራቸው ጎድጓድ ውስጥ ገብቶም ልባቸው ይቅርታን ሳይሆን የሚማፀነው በተቃራኒው ሀገርና ትውልድን ለመቅበር እየሞከሩ ነው::
ላለፉት 20 ምናምን አመታት በኢ/ት የፖለቲካ መድረክ ከፊት ሆነው ዛሬም እናውቅላችኃለን የሚሉን ስዎች እነዚያው የ60ዎቹ ትውልድ ሰዎች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን የሚገርመው የጥንት መናናቃቸውን ጥላቻቸውን እና ከዛሬው ትውልድ እድሜ በላይ ያስቆጠረውን ቂም በቀላቸውን በዚህኛው ትውልድ ህይወት ዋጋ ሊከፋፈሉ መታታራቸው ነው::
በጊዜ ብዛት መቀየር ያልቻለው የ60ዎቹ ፓለቲከኞች የማርክሲዝም ሌኒኒዝም (ማሌሊት) የፓለቲካ አስተሳሰብ ለአዲሱ ትውልድ የማይሆን እና ዘመኑን የማይመጥን መሆኑን በመረዳት ለትውልዱ ከመልቀቅ ይልቅ ሙጥኝ ብለዋል::
ለ27 አመታት መንግስት ሆኖ ባንክና ታንክ በመያዝ ታላቋን ሀገርና ህዝብን ሲነዳ የኖረው አሮጌው ህወሓት እና አዛውንት መሪዎቹ ከቤተ መንግስት ህይወት ከወጡ በኃላ ለዘመኑ ወጣት ቦታውን ከመልቀቅ ይልቅ ዳግም ወደ ስልጣን ለመመለስ የመንደር ጦርነት የጀመሩት ካረጀው የዚያ ዘመን አስተሳሰባቸው ባለ መላቀቃቸው ነው::
አብዛኞቹ የ60ዎቹ የፓለቲካ ሀይሎች እድሜ ዘመናቸውን እንዲሁ ሲያንቋርሩ እድሜያቸውን የጨረሱ በመሳሪያ ትግል ነፃ እናወጣዋለን ከሚሉት አካባቢ አንዲትን ወረዳ እንኳ መያዝ ያልቻሉና በስደት አለም በብርድ ሲጠበሱ የኖሩ መሆናቸውን በለውጡ ሰሞን ሰምተናል :: "ትግላችሁም ውጤት አላስገኘም : እናንተም በሰው ሀገር በስደትና በብርድ ልታልቁ ነው " ብሎ መንግስት በምህረት ያመጣቸው ሰዎች ውለው አድረው ጀግና ነን ሲሉና መንግስትን ይዋጣልን ሲሉት መስማት ይገርማል ::
የሆነ ሆኖ በዚያ ዘመን ብረት አንስተው ትግል ከገቡ ብዙ ፓርቲዎች መሀከል በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች እገዛ እድል ቀንቆት መንግስት መሆን የቻለው የዛሬው አማፂ ህወሓት በስልጣን ዘመኑ የፈለፈላቸውና አንዱን ፓርቲ ለሁለት : ለሶስት በመከፋፈል የሰራቸው የእጅ ስራ ውጤቶቹ እሱ ዳግም ወደ ሽፍትነቱ ከተመለሰም በኃላ " በቀለብ " ስለሚታገዙ ወላጃቸው ርቆ ሄዶም እነሱ የሽብር ስራውን ከመስራት አልቦዘኑም::
እናም መንግስት አሁን የጀመረውን ህግ የማስከበር እርምጃውን ጨክኖበት ዳግም አማፂነቱን ያወጀውንና ዋነኛውን የብጥብጥና የትርምስ ቡድኑን ማፅዳት ከቻለ "የሌላው እዳው ገብስ ነው" እንደሚባለው ይሆናል ለምን ቢባል ያለ ህወሓት ድጋፍ ወላ ሽኔ ወላ ኦነግ ወላ ምናምን አንዳቸውም አቅም አልባ ስለሆኑ::
የህወሐት ረዥም እጅ ከተቆረጠ ከጫፍ ጫፍ አትጠራጠሩ ሀገር ሰላም ይሆናል ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜም ያ የ60ዊቹ የፓለቲካ ነቀርሳ ከኢ/ት ላይ ዳግም ላይመለስ ይነቀላል : ይንቀለውናናናናና:


Follow Us