ጥጋበኛው የወያኔ ቡድን ህገ መንግስት ብሎ ላወጣው ህግ እንኳ መገዛት አቅቶት ሀገር ሲያተራምስ " እረ ተው " ያላሉት እና መጪውን ገምተው በሙያቸው መተንተን ያልሞከሩ የውጭ ሀገር የመገናኛ ብዙኃን መንግስት ህግ ላስከብር ብሎ ሲነሳ " ምነው ከህወሐት በላይ ተዋጊ በመሆን መንግስትን ወጠሩ " ?

እነ አልጀዚራ እንግሊዝኛ , ቢቢሲ አማርኛ , አሶሼትድ ፕሬስ ፍፁም ከጋዜጠኝነት ስነ ምግባር ውጭ ሚዛናዊ ባልሆነ ዘገባ ላይ ተጠምደዋል ::
የአልጀዚራው ዘጋቢ እንደ ልቡ በአ.አ ጎዳና እየተዘዋወረ ዜና ሲዘግብ በጠራራ ፀሀይ የተጠቀመው የቨድዬ ምስል ግን ፒያሳ ላይ የተቆለፈን የንግድ ሱቅ ነበር ::
ሲጀመር መንግስት ህግ ላስከብር ብሎ ከህግ በላይ ነኝ የሚለውን ወንበዴ ልክ ለማስገባትና ህግ ለማስከበር የተነሳው መቀሌ ላይ የሽመቀውን ቡድን ልክ ለማስገባት ነው ጦር ወደ ስፍራው ያዘመተው : ታድያ ምንም ኮሽታ በሌለባትና ህይወት በሰላም በሚጓዝባት አ.አ የሚገኘው የአልጀዚራው ዘጋቢ መሀመድ አዶ ምን ሆንኩ ብሎ ነው በእንቅስቃሴ ላይ ካሉ የንግድ ድርጅቶች ውስጥ የተዘጋውን መርጦ አለም እንዲያይለት የፈለገው ?
ሴኮ ቱሬ ጌታቸው መቀሌ ተቀምጦ በጦሩ ላይ የህወሀት ሀይሎች የፈፀሙትንና በጦር ወንጀለኛነት የሚያስጠይቀውን ቃለ ምልልስ ለድምፀ ወያኔ በአማርኛ የሰጠውን ቃለ ምልልስ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እየተረጎመ በየሰአቱ የሚያናፍሰው አልጀዚራ በጉዳዩ ዙሪያ በቀላለሉ መረጃ የሚሰጡ ሰዎች ባሉበት ከተማ ውስጥ ያለው ዘጋቢያቸው ለዘገባው ሚዛናዊነት ፍፁም አልተጨነቀምና አለመጨነቅ ብሽም ሳይሆን ሚዛናዊነት የሪፖርተሩም ሆነ የጣቢያው ፍላጎት ባለመሆኑ ተውት ::
ቢቢሲ አማርኛውም በተመሳሳይ የርስ በርስ ጦርነት በኢ /ት ተከፈተ : በየእለቱም ከ4 ሽህ በላይ ሰዋች ከኢትዬጽያ የመከላከያ ሀይል ጥቃት ለማምለጥ ሲሉ ወደ ሱዳን ድንበር እየሽሹ ነው ሲል በየእለቱ መቀመጫውን መቀሌ ያደረገው ዘጋቢዬ ነገረኝ እያለ ሚዛናዊነት የጎደለውን ዘገባ በብዛት ደጋግሞ አሰራጭቷል ::
በስመ ጋዜጠኝነት ከአመታት በፊት የምናውቃቸው የህወሐት ኢህአዴግ ባለሟሎችና ተከፋይ የውጪ ሀገር ሚዲያ ወኪሎች የአሁኑን ሁኔታ እንደ ወርቃማ እድል በመጠቀም ደሞዝ ከፋያቸውን ከሞት ለማዳን ሲሯሯጡ እያየን ነው::
አለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት በኢ/ት ስርጭታቸውን በተለያዩ ቋንቋዎች ለማስፋፋት ጥያቄ አቅርበው በተፈቀደላቸው ወቅት በተለይም ቢቢሲ ለአማርኛ : ለኦሮምኛና ለትግርኛው አገልግሎት የተቀጠሩ ሰዎች በብቃታቸውና በእውቀታቸው ሳይሆን ለፈቃድ ሰጭዋ ህወሓት የሚሰሩ ካድሬዎች መሆናቸውን ዛሬ ላይ ስናስታውስና የዛሬውን ምግባራቸውን ስንመለከት አስቀድሞውኑ ለተመለመሉበት አላማ መቆማቸውን እንገነዘባለን::
እናም በኢ/ት ውስጥ ቢሮ ከፍተው ወኪል ቀጥረው የሚዲያ ስራ እንዱሰሩ ፈቃድ የሰጠው የብሮድ ካስት ባለስልጣን የነዚህን የጥፋት ነጋሪት ጎሳሚ ሚዲያዎችን ፈቃድ ካልሰረዘና አንድ ካላላቸው በቀር ህዝብን በህዝብ ላይ የሚያስነሳ ዘገባን ከማሰራጨት አይቆጠቡምና በፍጥነት እርምጃ መውስድ ቀዳሚ ተግባሩ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ::


Follow Us