በዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ በቋሚነት ከወደ መቀሌ ከምንስማው የዶ/ር ደብረፅዬን ፉከራ በተጨማሪ በአልፍ ገደም የሚሰማው የአማራ ብሔር ተወላጅ ሆኖ ሳለ በብቸኝነት የህወሐት አባል ስለሆነው ስለ ሴኮቱሬ ጌታቸው ጉዳይ ነው :: 

ወሬውም " ሴኮቱሬ በህወሕቶች ተገደለ የሚል ነው "

የወሬውን እውነትነት ማረጋገጥ ባይቻልም ግን " ሴኮ " ነገር አሳመርኩ ብሎ ከተናገረው ንግግር በመነሳት ነገሩን መጠርጠር ይቻላል :: ለምን ቢባል የሴኮቱሬ ንግግር ህወሓትን በአለም አቀፍ ወንጀል የሚያስጠይቅ መረጃ በመሆኑ ህወሓትን ሊያስቆጣ ስለሚችል መጠርጠራችን ልክ ሊሆን ይችላል::
የኢ/ት መንግስት ትግራይ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ " የትግራይ ልዩ ሀይልና ሚሊሽያ "
በለሊት ጥቃት በማድረስ በጦሩ ላይ አስነዋሪ ጭፍጨፋ ማድረሱን ይፋ በማድረግ ጉዳዩን አለም እንዲያውቅና ህግ ለማስከበር ሲል ተገዶ ወደ ጦርነት መግባቱን ለተናገረገው መረጃ ነው ሴኮቱሬ ጌታቸው በድምፀ ወያኔ ቴሌቭዥን ቀርቦ የመንግስትን ክስ እውነትነት በይፋ ያረጋገጠው ::
ወያኔ በረሀ እያለችና ከደርግ ጋር ስትዋጋ "አንድ የወልዲያ እናት ያላቸውን አንድ እንቁላል ለጀግናው የህወሀት ሰራዊት ለገሱ " ይል የነበረው የፕሮፖጋንዳ ማሽኑ ሴኮቱሬ ጌታቸው ስለ ዘመን ለውጥ ምንም ባለማወቁና ድንቁርናው ዛሬም ሳይለቀው በሽምቅ ተዋጊነት ወቅት የነበረውን አስተሳሰብ እና የፕሮፖጋንዳ መንገድን በመከተሉና ንግግሩ የሚያመጣውን ጦስ ባለማወቁ " ፈውል" ቢገባ ምን ይገርማል ትላላችሁ?
ሙላው የወያኔ አመራር ከ40 አመታት በፊት በነበረው አስተሳሰብ ላይ የተቆለፈ የደንቆሮ ስብስብ በመሆኑና "ሴኮ ነብሴም" በተቆለፈበት የድንቁርና አስተሳሰቡ ውስጥ በመሆኑ ነገር ያሳመረ መስሎት ባደረገው የድንፋታ ንግግሩ በወያኔ ቢበላ ምን ይደንቃል ?
ሲጀመር ወያኔ የትግራይ ነፃ አውጭ ነኝ ብላ በረሀ ስትገባ እና በብሔር ስትደራጅ አማራው ሴኮቱሬ ጌታቸው አማራነቱንና ማንነቱን በመካድ የህወሐት አባል ለመሆን መወሰኑን ስናስብ በራሱ የሰውዬውን ውዳቂነት የሚያጋልጥ ተግባር አይመስላችሁም ?
ሳያስቡት ጦርነት ጀምረው ድንገት የመቀሌ ዙሪያ ገባው ገደል የሆነባቸው የህወሐት አዛውንቶች የጭንቅ መንገድ በሚማጠኑበት ሰአት ደንቆሮው ሴኮ በቴሌቭዥን ቀርቦ " የሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊትን ድንገት በመውረርና ቀድመን መብረቃዊ ጥቃት በመፈፀም በ45 ደቂቃ ውስጥ እንዳይሆን ባናደርገው ኖሮ አሁን እንዲህ ተቀምጠን ማውራት አንችልም ሲል መናገሩ በህወሐቶች ዘንድ ሆን ብሎ ሊያስበላን በመፈለጉ ነው የሚል ጥርጣሬ ፈጥሮስ ቢሆን ቀድመው ህወሓቶች የበሉት ?
ለማንኛውም በደንቆሮው ሴኮቱሬ ጌታቸው ዙሪያ የተሰማው ወሬ ለጊዜው እርግጡ ባይታወቅም ግን እጣ ፈንታው ከሁለት አንዱ ነው እንደተባለው ወይ በህወሐት ተበልቷል አሊያም በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ ከመውደቅ የሚያድነው ስለመኖሩ እንጃ ?


Follow Us