ከዛሬ 30 አመት በፊት ወያኔ ከደርግ ጋር ስትዋጋ ፍፁም የሀገር ጠላት የሆነ ሌላ ወራሪ ምናልባትም የማያደርገውን የጥፋት ድርጊት ትፈፅም እንደነበር ያፈረሰቻቸውን ድልድዬች መቁጠሩ በቂ ይመስለኛል ::

ወያኔ ለህዝብ ነፃነት እታገላለሁ እያለች ነገር ግን ህዝብ የሚጓጓዝበትን ድልድይ ማፍረስ : ሆስፒታሎችን ማቃጠልና ማውደም : ደሀው ያስቀመጠውን ገንዘብ ከባንክ መዝረፍ : ለተራቡ ህጻናት የተላከን የእርዳታ ስንዴ ወዘተ ወዘተ መዝረፍ ዋነኛው የህወሐት እና የደንቆሮ መሪዎቿ ምግባር ነበር ::

እናም ከ30 አመታት በፊት ወልዲያ አቅራቢያ በተራራ መሀል የሚገኘውን "ዶሮ ግብርን" ጨምሮ በወሎ አካባቢ የሚገኙ ሌሎች ድልድዬችንም ማፍረሱ ይታወሳል ::

የወያኔን የጥፋት መልዕክተኝነት በደንብ የተረዳው ደርግ ያኔ ወያኔን "ድልድይ አፍራሽ" እያለ መጥራቱን ዛሬ ላይ ስናስብ በርግጥም በትክክል እንደሰየማት እንረዳለን ::

ያለ አቅሟ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የደፈረችው ወያኔ ዙሪያ ገባዋ መጥበቡን ስትረዳ የጥንት ልምድና ስራዋን ተግባራዊ በማድረግ የመቀሌ መግቢያ ዙሪያ መብገዶችን በአራቱም አቅጣጫ በትራክተር አረሰችው ::

በዚህ ዘመን ግጭት እና ጦርነት አይጀመር እንጅ እንኳንስ እንደ ወያኔ ላለች ጭባ ታጣቂ ይቅርና ከ100 ሚሊዬን በላይ የሆነ ህዝብን ከየትኛውም ወራሪ ለመጠበቅ ሙሉ ሀይል የታጠቀው የኢ/ት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሌሎችም አይተኛም እና ወያኔ መሽሽግያ ይሁነኝ ብላ ሀገር ብትቆፍርም ጉድጓዱ መቀበሪያዋ ይሆናታል እንጅ ሰራዊቱን ከመንገዱ አይገታውም::

ወያኔ በረሀ እያለች የአድዋ ባንክን ጨምሮ ሌሎችን የህዝብ የገንዘብ ተቋማትን ስትዘርፍ እና ከውሀ ሙላት ህዝብ ከሚጠበቅበትና መውጫ መግቢያው የሆነን የኑሮ መሰረቱ የሆነውን ድልድይ ስታፈርስ ነገ ተሳክቶልኝና ትግሌ ሰምሮ መንግስት ብሆን የኔው የቤት ስራ ይሆናል ብላ አለማሰቧ እና ሀላፊነት ውስጥ አለመውደቋ የመሪዎቿን ድንቁርና ይናገራል::

እና ወያኔ ዛሬም በለመደችው የድንቁርና መንገዷ በመጓዝ የደደቡ መሪዎቿ የማያዋጣቸውንና አጓጉል በሆነ የትዕቢት ትንኮሳቸው ለአመታት ደጃቸውን ሲጠብቅ እንዳልኖረና እንዳልተጋባቸው በለሊት የጭካኔ በትራቸውን በሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ላይ ካሳረፉ በኃላ ምላሹን መቀበል ቢከብዳቸው ድልድይ ማፈራረስ ጀመሩ::

መቼም ካፈርኩ አይመልሰኝ ባይዋ ወያኔ በቆፈረችው ጉድጓድ ካልተቀበረች በቀር ለሀገርም ለህዝብም ሰላም አይሆንምና ከጀግናው ክንድ ያድነኝ ብላ በቆፈረችውና በመቀሌ መግቢያ ዙሪያ ባዘጋጀችው ጉድጓድ የተነኮሰችው ሰራዊት ቶሎ ግባ መሬቷን ያጣድፍላትና ይገላግለን :: የሆነ ሆኖ ግን ወያኔ አሁን ያደረገችው ነገር ምንም የማናውቀውና አዲስ ነገር አይደለም የኖረችበትና የምትኖርበት እውነተኛ ህይወቷ ክውን ድልድይ ማፍረስ አይድነቀን ለማለት ያህል ነው:: ቸር ያሰማን ::


Follow Us